በማዕከላዊ ንጽኋን ታሳሪዎችን የሚያሰቃዩ የማዕከላዊ መርማሪዎች ተጋለጡ👉these Tplf mafia group 👉 killing , torturing, innocent civilians in Ethiopia

በማዕከላዊ ንጽኋን ታሳሪዎችን የሚያሰቃዩ የማዕከላዊ መርማሪዎች ተጋለጡ

እነዚህ ጨካኝ መርማሪዎች በንጽሀኖች ላይ ቶርቸር ፣እስራት ፣ድብደባን ምርመራ በሚል ሽፋን ከፍተኛ ኢ-ሰብአዊ የመብት ጥሰት የሚፈጸሙ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው ኮማንደር ሙኒ፣ ኮማንደር ወንድሙ የተባሉት የህወሃት ቅጥረኞች በታዋቂ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የሀይማኖት አባቶች እጅግ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ስቃይና ድብደባን በማእከላዊ ሲፈጽሙ የነበሩ ናቸው።ወደፊት በሀገራችን ፍትህ ሲሰፍን ከተጠያቂነት የማያመልጡ በመሆናቸው እንዲሁም አሁንም ባሉበት ህዝብ ማንነታቸውን አውቆ በማህበራዊ ህይዎትም በማግለል እነዚህን ጨካኞች ሊቀጣቸው ይገባል ሲሉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
እኩይ ድርጊታቸውን አጠናክረው ለመቀጠልም ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ስብሰባ አድርገዋል።በዛሬው እለት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ጋር ብሔራዊ ደ34rህንነት ምክር ቤት በዝግ ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።ከስብሰባው በሁላ በኢቢሲ እንደተገለጸው በቀጣይ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎችን ለማርገብ በሚል aaርምጃ ለመውሰድ ማቀዳቸው ታውቋል።እነዚህ ጨካኝ መርማሪዎችም ይህንኑ ግፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ነው ስብሰባውን ያደረጉት።በፎቶው ላይ ያሉትን ጨካኝ አረመኔዎች ሁሉም እንዲያውቃቸው ፎቶና መረጃውን ሼር ፖስት በማድረግ ያስተላልፉ
በማእከላዊ አረመኔያዊ ተግባር የሚፈጽሙት እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹንም በቀጣይ ጊዜ እየተከታተልን የምናጋልጥ ይሆናል ።