ወያኔ የሚያሳቃያት ጀግናዋ ጫልቱ ታከለ

ወያኔ የሚያሳቃያት ጀግናዋ ጫልቱ ታከለ፣

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእስር ላይ የምትገኘው ጫልቱ ታከለን በገንዘብ ቀጥቷል።ጫልቱ ታከለ ከዚህ ቀደም በወያኔ መነግሥት
8አመት ከአንድ ወር ታስራ ስትሰቃይ የነበረች የኦሮሞ
ልጅ ናት።ከእሥር ተፈትታ በስድስት ወሩ ደግሞ “ወደ
ኤርትራ ለመሄድ ሞክራ ታያዘች” የሚል ክስ ቀርቦባት
ከታሰረች ሰነባብቷል።
ትናንት ህዳር 28/2010 ዓ.ም (ዴሰምበር 7/2017)እነ ደቻሳ ሞሲሳ ተከላከሉ የሚል ብይን በተሰጠባቸው ወቅት 3ኛ ተከሳሽ የሆነችው ጫልቱ በሰነድ ማስረጃነት የቀረበባት የደህንነት ሪፖርት ወደ ኤርትራ ስለመሄድ የጠቀሰው ነገር ሳይኖር ብይን ላይ ወደ ኤርትራ ልትሄድ እንደነበር ተጠቅሶ ተከላከይ መባሏ እንዳሳዘናት ገልፃለች።

ጫልቱ ታከለ በወቅቱ “ከኢህአዴግ ፍርድ ቤት ምንም አንጠብቅም። ወደፊትም ከዚህ ችሎት ፍትህ እንደማናገኝ ነው ፣የማስበው ” ብላ በመናገሯ በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ተብላ በአዳር ዛሬ ህዳር 29/2010 ማለትም ዴሰምበር
8/2017 ፣የ500 ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባታል።
ጫልቱ ታከለ ማን ናት?
ምሥራቅ ወለጋ የተወለደችው ጫልቱ በሽብርተኝነት ሰበብ
በግንቦት 2000ዓ/ም ከፍንፍኔ ዩንቬርስቲ በወያኔ ደህንነቶች
የኦሮሞ ተማሪዎች እየታፈሱ እንዲታሰሩ ስደረግ ከታሳሪዎቹ ውስጥ አንዷ ጫልቱ ናት። በዚያን ወቅት ጫልቱ የ2ኛ አመት የሶሾሎጂ ተማሪ ነበረች።
በወያኔ ደህንነቶች እጅ ከገባች ቦኋላ ብዙ ስቃይ ያየችው
ጀግና ተገርፋለች፣በዘሯ ተሰድባለች፣ በጨለማ ቤት ታስራለች፣ስንቅ እንዳይደርሳትና ቤተሰብ እንዳይጠይቃት
ተደርጓል።በ2000 ዓ/ም ስትታሰር፣ገና አሥራ ስምንተኛ አመቷን ያልጨረሰችው ለጋ ልጅ ጥፋቷ ኦሮሞ መሆን ብቻ
ነው።ጫልቱ ጎበዝ ተማሪ፣አንደበተ ሪቱዕ ፣አስተዋይ፣
ትክክለኛ ታሪኮችን መስማት የሚትወድ፣በማይመስላትና
ውሸት በሆኑ ጉዳዮች የማትስማማ ፣ከሁሉም ባላይ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም በሚነካ ጉዳይ ለመቃወም የማትፈራ ስለመሆኗ ጓደኞቿ ይናገራሉ።
በዚሁ ምክንያት ከዚህ ቀደም 12 አመት ተፈርዶባት በአማክሮ 8 አመት ከአንድ ወር ታስራ ከተለቀቀች ቦኃላ
እንደ ገና በስድስተኛ ወሩ አሰረዋታል።

ስለ ጫልቱ አብረዋት በወያኔ እሥር ቤቶች የነበሩ ፀጠሐፊዎችና ብሎገሮች፣የመብት ታጋዮች ምን ይላሉ???

“……ከማዕከላዊ ማጎሪያ ቤት ፍርደኛ ሆኜ ወደ ቃሊቲ
ማጎሪያ ስገባ ከገኘኋቸው ቆራጥ የህዝብ ልጆች አንዷ
ጫልቱ ታከለ ናት።እውነት ለመናገር ስለዚህች ብርቱ ሴትና
ከሷም ጋር በኦነግ ስም ተከሰው እየተሰቃዩ ስላሉት ጠንካራ ወጣት ሴቶች ያወኩት ቃሊቲ ታስሬ ነው።8 አመት አሰቃይተዋትም ተስፋ የማትቆርጥ፣በገኘችው ሁሉ የወያኔን
ዘረኝነትና ስለወደፍታቸውም አስከፊነት የሚትናገር ናት።
ሁሌም የአገዛዙ ፖሊሶች አይወዷትም፣ይፈሯትና ይጠሏታል።
ለእስረኞች ደግሞ በጭንቃቸው ጊዜ አማካሪ፣አጽናኝ፣
አስተማሪም ናት።8አመት አንድን ሴት ያለ ጥፋት አስሮና አሰቃይቶ እንደገና ማሰር ምን አይነት ጭካኔ እንደሆኔ አይገባኝም።በማዕከላዊ ስትገረፍ፣ስትሰቃይ ቆይታ አሁን ወደ ቃሊቲ መዛወሯን ሰማሁ።…..በዚህ ጊዜ ይህንን አገዛዝ
ለመቃወምና በቃህ!ለማለት፣የፖላቲካ ፖርቲ አባል መሆን የግዴታ አይደለም፣ተዋቂና ምሁር መሆንም አይጠበቅም፣
…. ሰዉ ብቻ መሆን በቂ ይመስለኛል።ስለ ተደፈሩት፣ስለተገደሉት፣ስለተዋረዱትና ስለ ተሰቃዩት እህቶቻችንና ወገኖቻችን የደረሰባቸውን ግፍ መቃወምና መናገር ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው!!..”
# ሜሮን አለማዬሁ በግንቦት ሰባት አባልነት ተጠርጥራ
ከጫልቱ ጋር ታስራ የነበረችው ከሰጠችው እስተያዬት#
(Ethiopian exploler ዴሰምበር2017)

ታዋቂ ፀሐፊ፣ብሎገርና የወያኔን ፖለቲካ በማጋለጥ የተካነችው፣ ማህሌት ፋንታሁን በአማርኛ ገጾች ላይ
29 February 2016 ስለ ጫሊቱ የሚከተለውን ጽፋለች፤
“……በቀጠሮ ላይ የነበረን እና ፍርደኛ ሴት እስረኞች በተለያዬ ግቢ ስለምንኖር፣ከጫሊቱ ጋር በሰፊው ለማውራት
ዕድል አላጋጠመኝም፤ቤተሰብ ልጠይቀን ሲመጣ፣እዚያው
በምንገናኝበት ጥቂት ደቂቃዎች ስናዋራ…ጫልቱ ቆራጥ፣
ስለ መብቷ ለመናገር ማንንም የማትፈራ፣ደፋር እና ጠንካራ
ሴት መሆኗን አይቻሌሁ፣ሰምቻለሁም..”

የኛዋ ጀግና እንደዚህ አይነት ሰው ነች!!!

VIA Melkamu Temesgen