ህወሓት/ኢህአዴግ ባለፉት ሦስት አመታት ብቻ፤ ከ1200 በላይ ግለሰቦችን ገድሏል፤ በሺህዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል፣ ከ700 ሺህ በላይ ደግሞ ከመኖሪያ ቤታቸው አፈናቅሏል። አሁንም ቢሆን በዜጎች ሕይወት፥ አካልና ንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳትና ጥቃት ቀጥሏል። ይሄን ሁሉ ግፍና በደል በዜጎች ላይ የፈጸሙ፣ እንዲሁም ሲፈፀም ዳር ቆመው ሲመለከቱ የነበሩ የመንግስት ኃላፊዎች፥ የፀጥታና ደህንነት ኃላፊዎች፣ የጦር ጄኔራሎች፣ ወታደሮች፥ ፖሊሶች፥ ታጣቂዎች፥…ወዘተ ዛሬም ድረስ ዜጎችን ይገድላሉ፥ ያቆስላሉ፥ ያስራሉ፥ ያሰቃያሉ። እንደ ከዚህ ቀደሙ አሁንም “የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር” የሚል ሰበብ ያቀርባሉ። ዛሬም “መንግስት” እንደሆኑ፣ ሕዝብና ሀገር እንደሚመሩ ያስባሉ፥ ይናገራሉ፥ ይሰብካሉ። የኢትዮጲያ ሕዝብ ሰላምና ደህንነቱን ያጣው የመጀመሪያውን ንፁህ ዜጋ በግፍ የገደሉ ዕለት ነው። መንግስት የወደቀው በሕዝብ ስም ዜጎችን የገደለ ዕለት ነው! ኢትዮጲያዊያን ሀገር-አልባ የሆኑት ከዚያን ዕለት ጀምሮ ነው!

via መንግስት የሚወድቀው በህዝብ ስም ዜጎችን ሲገድል ነው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s